አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት የተነሳ ጋዛ ውስጥ የተፈጠረው የነዳጅ እጥረት በእንስሳት የሚጎተቱ ጋሪዎችን በስፋት ለመጓጓዣነት እንዲውሉ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።
በጋዛ አሁን ላይ የጭነት እንስሳት ጋሪ ሲጎትቱና ሰው ሲያመላልሱ እንዲሁም እቃ ጭነው ከአንድ ሥፍራ ወደ ሌላ ሥፍራ ሲያደርሱ መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡
የጋዛ ነዋሪዎች በተለይ የተገኘውን ውሃ በጋሪዎቻቸው በመጫን ለአገልግሎት እንደሚያውሉትም ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
ከአል-ዛና ተፈናቅሎ ጋዛ የከተመው ማኸር ሻሂን የተባለ ግለሰብ ግጭቱ ከተጀመረ ወዲህ “ሕይወት በጋዛ አክትሟል” ሲል ይናገራል።
ልጆቹን እንኳን መመገብ እንዳቃተው ነው የገለጸው፡፡
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት እስካሁን 11 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ለሕልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
#Israel #Hamas
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!