አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ የመንግሥት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ማዕከላት መሰጠት ተጀምሯል።
በጅማ ስልጠና ማዕከል የመክፈቻ ሥነ- ስርአት የተካሄደ ሲሆን፥ በስልጠናው ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 2 ሺህ የሚሆኑ የመንግስት አመራሮች እተሳተፉ ነው፡፡
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በወላይታ ሶዶ ስልጠና ማዕከልም መሰጠት ተጀምሯል ።
በተመሳሳይ በስልጠናው ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 2 ሺህ የሚሆኑ የመንግስት አመራሮች የሚሳተፉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በዲላ ማዕከልም “ከእዳ ወደ ምንዳ “በሚል መሪ ቃል ለመንግሥት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት የተጀመረ ሲሆን፥ ከ1 ሺህ 200 በላይ አመራሮች ስልጠናውን እየተከታተሉ መሆኑ ተመላክቷል ።
የመንግስት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በተመሳሳይ በአምቦ የስልጠና ማዕከል፣ በሀረማያ የስልጠና ማዕከል ፣በወሎ የስልጠና ማዕከል፣ ሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ ማዕከል እንዲሁም በጅግጅጋ ከተማና በሌሎችም ከተሞች በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው ለ12 ቀናት እንደሚቆይ ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡