Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል የመሪ ቃል ትንተና ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ብዝኃነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ ለሚከበረው 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል የመሪ ሐሳብ ትንተና ተካሂዷል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በዓሉ ከሕዳር 25 እስከ ሕዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በሶማሌ ክልል በድምቀት ይከበራል ብለዋል።

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውን እና ባሕላቸውን በመለዋወጥ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ በማድረግ ለዘላቂ ሰላም፣ ልማት እና ኢኮኖሚ ዕድገት እንዲነሳሱ ማድረግ የበዓሉ ዓላማ ነው ብለዋል፡፡

በዓሉ ሲከበር በሕዝቦች መካከል አንድነት ስር እንዲሰድ እና እንዲዳብር ለማድረግ የብዙኃን መገናኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልጸው በዚሁ ልክ እንዲሠሩም ጠይቀዋል፡፡

በመሪ ቃሉ የትንተና ሠነድ ላይ የሁሉም ክልል አፈ-ጉባዔዎች እና ብዙኃን መገናኛ ተገኝተዋል።

በፈቲያ አብደላ

Exit mobile version