Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሠራዊቱ በሶማሌ ክልል በጎርፍ ለተጠቁ የህብረተሠብ ክፍሎች የምግብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በሊበን ዞን በዶሎ አዶ እና በአካባቢው በሚገኙ ወረዳዎች በጎርፍ ለተጠቁ የህብረተሠብ ክፍሎች የመከላከያ ሠራዊት የደረቅ ምግብ ድጋፍ አደረገ።

በስፍራው ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ኮሎኔል አየለ ቢፍቱ፥ በተደጋጋሚ ከመጠን በላይ ያለፈ ዝናብ ከመዝነቡ ጋር ተያይዞ የዳዋና የገናሌ ወንዞች ሞልተው ከተማውን በማጥለቅለቃቸው ምክንያት ለ3 ሺህ 500 ነዋሪዎች ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ሆኖም አሁንም በጎርፉ ለተፈናቀሉ ወገኖች ተጨማሪ የምግብ ድጋፍ ማስፈለጉንም ነው የገለጹት።

የኮር የሠራዊት አባላት ወንዝ ተሻግረው የሎጅስቲክስ አቅርቦት በመኪና ማድረስ ባለመቻላቸው በጊዜያዊነት የአቅርቦት ክፍተትን ለመሸፈን ህዝቡም በጀልባው እየተገለገለ መሆኑንም ተናግረዋል።

ችግሩ ከተከሠተ ጊዜ ጀምሮ ሠራዊቱ 320 ካርቶን ደረቅ ምግብ ድጋፍ ያደረገ መሆኑንም ነው የጠቀሱት፡፡

በአሁኑ ወቅትም ሠራዊቱ በህዝብ ላይ በሚያጋጥመው የሠው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ፈጥኖ በመድረስ ህዝባዊነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version