አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ‘ውመን ኢን ኒውክሌር ግሎባል እና ውመን ኢን ኒውክሌር አፍሪካ’ የተሰኙ ሁለት ዓለም አቀፍ የሙያ ማህበራትን ተቀላቀለች፡፡
በአስዋን ግብፅ እየተካሄደ በሚገኘው ‘ዊን ግሎባል ኮንፈረንስ’ ኢትዮጵያ የተቋማቱ አባል እንድትሆን ባቀረበችዉ ጥይቄ መሰረት በራዲየሽን እና ኒውክሌር ዘርፍ ሴቶች ላይ በማተኮር የሚሰራ ‘ዊን ኢትዮጵያ’ የተሰኘ ማዕቀፍ በማስጀመር ተቀላቅላለች፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር)፥ ‘ ዊን ኢትዮጵያ’ ሴቶችን በጨረራ እና ኒውክሌር ዘርፍ አቅም በማጎልበት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው አስረድተዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ‘የዊን ኢትዮጵያን’ አላማ በመደገፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርጋል ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።