Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሆሮ ጉድሩ ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያለመ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማምጣት ያለመ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት በሆሮ ጉድሩ ዞን ተካሂዷል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ የተገኙት የዕዙ ምክትል አዛዥ ሜ/ጄ ነገሪ ቶሌራ÷ በሰላምና በፍቅር የኖሩትን ሕዝቦች ግጭት ውስጥ በመክትተ ለፖለቲካዊ ትርፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ፅንፈኞች በንፁሃን ላይ የሕይወትና የንብረት ጥፋት ሲያደርሱ መቆየታችውን አስታውሰዋል፡፡

በአካባቢው ለዘመናት አብረው የኖሩት የዞኑ ሕዝቦች በቀጣይ የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ወደ ልማት መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊቱ ከገባ ጀምሮ የተገኘውን ሰላም በማስጠበቅ ወደ መሰረተ ልማት ስራ ለማስገባት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

እርቁ በሆሮ ጉድሩ ዞን በአምሩ ወረዳ ይፈጠሩ የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል ያስችላል መባሉንም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

በእርቅ ሥነ-ሥርዓቱ ከፍተኛ የሰራዊቱና የዞኑ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከሕብረተሰቡ የተውጣጡ የሀገር ሸማግሌዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Exit mobile version