Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለእውነተኛ ሠላም መንግሥትና ሕዝብ በጋራ እየሠሩ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለእውነተኛ ሠላም መንግሥት እና ሕዝብ በጋራ እየሠሩ መሆኑን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የውይይት መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ÷ የደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች አጠቃላይ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ለእውነተኛ ሠላም መንግሥት እና ሕዝብ በጋራ እየሠሩ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህ ስኬታማነትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው÷ ጊዜው በተናጠል ሳይሆን ለሁለንተናዊ ደኅንነታችን በጋራ የምንሠራበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በቅንጅት ያሉብንን ችግሮች ተሻግረን የሕዝባችንን ጥያቄ ልንመልስ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመድረኩ በክልሉ ብሎም አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version