Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት ሀገራዊ ምክክር ወሳኝ በመሆኑ ተሳትፎን ማጠናከር ይገባል – የፖለቲካ ፓርቲዎች

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አንድነትን የሚያጠናክር አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት ሀገራዊ ምክክር ወሳኝ በመሆኑ ተሳትፎን ማጠናከር ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ በወል ዕውነቶች ላይ የተመሰረተ አሰባሳቢ ትርክት መገንባትት ይገባል።

ለዚህ ደግሞ የምሁራን፣ የፖለቲካ ልሒቃን፣ የመንግሥትና ሕዝብ ኃላፊነት የላቀ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባል መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር)÷ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላምና አንድነት ለማስፈን ከጥላቻና መገፋፋት ፖለቲካ መውጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በሰንደቅ ዓላማ፣ በታሪክ፣ በትርክት ለምን እንጋጫለን ያሉት መብራቱ (ዶ/ር) በመሰል ጉዳዮች ላይ በኃሳብ ተከራክረን፣ ተነጋግረን ተወያይተን ለሀገር የሚበጅ ነገር ላይ መድረስ አለብን ነው ያሉት።

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑም አሰባሳቢ ትርክት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ሁላችንም ተሳትፏችንን ልናጠናክር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የሕብር ዴሞክራሲ ፓርቲ መሥራች አባል ጸገነት ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ጠቃሚ ትርክቶች ይልቅ ጎጂ ትርክቶች ቦታ እየያዙ በመምጣታቸው ዋጋ እየከፈልን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት ምክክርን ያስቀደመ አካሄድ ወሳኝ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version