Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጥያቄ በመንግስት ብቻ የሚመለስ ሳይሆን የግሉ ዘርፍ ትብብርን ይጠይቃል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጥያቄን ለመመለስ ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር መስራት እና የግሉን ዘርፍ ማበረታታት እንደሚጠይቅ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ኖህ ሪል ስቴት በዛሬው ዕለት የገነባቸው 754 መኖሪያ ቤቶች የተመርቀዋል።

ኖህ ሪል ስቴት ለከተማ ነዋሪዎች ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት የተገነቡ 5 ሺህ ቤቶችን ጨምሮ እስከአሁን ከ8 ሺህ 600 በላይ ቤቶችን ገንብቶ ማስተላለፉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ቤቶች በጥራት መገንባታቸውን እና የበርካታ ነዋሪዎችን የቤት ችግር የሚቀርፉ መሆናቸውን ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩም መኖሪያ ቤቶች ለከተማዋ ዕድገትና ለነዋሪው ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ በመኖሪያ ቤት ላይ ለተሰማሩ ኩባንያዎች የሚያደርገውን ድጋፍ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

Exit mobile version