Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለ28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።
 
በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ ውስጥ ከሕዳር 20 እስከ ታህሳስ 2 የሚካሄደው ጉባኤው በሶስት ምዕራፎች የተከፈሉ የተለያዩ ክንውኖች እንደሚኖሩትም ተጠቁሟል።
 
በጉባኤው የመጀመሪያ ሁለት ቀናትም ከ120 በላይ ሀገራት መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
ኢትዮጵያም በአረንጓዴ አሻራ፣ በስንዴ ልማት፣ በምግብ ስርዓት ላይ የሰራቻቸውን ስራ በተመለከተ በዓለም አቀፍ መድረኩ ላይ ተሞክሮዋን እንደምታካፍል ይጠበቃል።
 
በተጨማሪም በጉባኤው በተለያዩ ጊዜያት በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ ታዳጊ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ የተገቡ ቃሎች ትግበራ ላይ ምክክር እንደሚደረግም ተነግሯል።
 
በተጎዳኝ የሚደረጉ የሁለትዮሽ ውይይቶችም ይጠበቃሉ።
 
በትዕግስት ብርሃኔ
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version