አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ109 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የ2016 የመጀመሪያ ሩብ በጀት ዓመት የመንግሥት የሥራ አፈጻጻም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ኤፍ ቢ ሲ) በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እንደተናገሩት፥ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 529 ቢሊየን ብር ግብር ለመሰብሰብ እቅድ ተቀምጦ እየተሰራ ነው፡፡
ከዚህም ውስጥ 110 ነጥብ 3 ቢሊየን ብሩን በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለመሰብሰብ ታቅዶ፤ 109 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 99 ነጥብ 2 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎች እንዲሁም ጥብቅ የክትትልና የቁጥጥር ስራ ተግባራዊ መደረጉ ለእቅዱ መሳካት ዓይነተኛ ሚና መጫወታቸውንም ነው ያስረዱት።
በሩብ ዓመቱ የታየው አፈጻጸም በዘርፉ ያለውን አሰራር ማዘመንና የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን በማጠናከር የዓመቱን እቅድ ማሳካት እንደሚቻል ያመላከተ ነውም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ገቢ የመሰብሰብ አቅም አሁንም ይበልጥ ማደግ እንደሚችል ማሳያ መሆኑንም ነው አክለው የገለጹት፡፡
ከዚህ አኳያ በቀጣይ በተለይ የግብር አሳበሰቡን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በግምገማው አቅጣጫ መቀመጡን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!