Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ ቡዜና አልከድር የጉባዔውን አጀንዳዎች አስተዋውቀዋል።

አጀንዳዎቹም ፦

1ኛ. የምክር ቤቱ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ማጠቃለያ ጉባዔ ቃለ-ጉባዐየን ተወያይቶ ማጽደቅ

2ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ማዳመጥ

3ኛ. ልዩ ልዩ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ እና

4ኛ. ልዩ ልዩ ሹመቶችን ተወያይቶ ማጽደቅ የሚሉት መሆናቸውን በማስተዋወቅ ጉባዔውን ማስጀመራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጉባዔው ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አሥተዳደሩን የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያቀርቡም ተጠቅሷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version