አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ከ336 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ8 ወረዳዎች ለሚገነቡ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተደድር ደስታ ሌዳሞ በጎርቼ ወረዳ በ41 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገነባውን የ”ሶካ ሶኒቾ አሳራዶ ዳማ” የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሥራ አስጀምረዋል።
የሶካ ሶኒቾ አሳራዶ ዳማ ፕሮጀክት በሁለት ቀበሌዎች የሚኖሩ 7 ሺህ 200 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል።
የውሃ ፕሮጀክቶቹ በክልሉ መንግስት በጀት እና በአጋር አካላት አማካኝነት የሚከናወኑ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።