Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ328 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 328 ሚሊየን 478 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የክልሉ ሀብት ማሰባሰቢያና የክልሉን ፀጋዎች ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ ተወላጆችና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የሕዝብና የልማት አጋሮችን አቅም በማቀናጀት የክልሉን ሕዝብ አጠቃላይ የልማት ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ተስፋ ለአዲስ ክልል በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የሀብት ማሰባሰቢያና የክልሉን ጸጋዎች ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይ 328 ሚሊየን 478 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

Exit mobile version