አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከብሪክስ ሀገራት የተወጣጡ ዳኞችን ያካተት ሴሚናር በቻይና ቤጂንግ እየተካሄደ ነው፡፡
በሴሚናሩ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ፉአድ ኪያር የተመራ የሶስቱም የፌዴራል ፍ/ቤቶች ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የብራዚልና የግብጽ ዳኞችን ጨምሮ ከሀገራቱ ፍትሕ ሚኒስቴር የተወከሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡
በኢትዮጵያም ከፍትሕ ሚኒስቴር የተወከሉ ዓቃቤያን ሕጎች እየተሳተፉ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መረጃ ያመለክታል።