Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የጤና አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች እንዲሁም ከአጋሮች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ዜጎች የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን÷ ኢንዱስትሪ ፓርኮችም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሰራተኞች የጤና አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ ያግዛል ተብሏል።

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በሥነ-ስርዓቱ ላይ÷ የሰነዶቹ መፈረም መንግስት ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የስራው ባለቤት በዋናነት ክልሎች በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም ማሳሰባቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም÷ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ማግኘት መቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡

Exit mobile version