አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሰራባ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ 230 ህገወጥ የቱርክ ሽጉጥ መያዙ ተገለፀ።
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው ከሼህዲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ኒሳን ፓትሮል ሲንግል ሚኒካፕ በሆነ የግል መኪና ላይ በትናትናው ዕለት በሰራባ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ነውየተያዘው።
ከዚህ ጋር ተያይዞም አንድ ተጠርጣሪ የህገ ወጥ የጦር መሳሪያውን በማዘዋወር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ነው ከጭልጋ ወረዳ የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለከተው።
ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ በጉምሩክ ፍተሻ በተደጋጋሚ እየተገኘ በመሆኑና ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ወደ ክልሉ እየገባ በመሆኑ ይሄን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርም በጉምሩክ ፍተሻ ብቻ መቆጣጠር ስለማይቻል በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅርና ማህበረሰቡ ትብብርና ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።