Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

96 ዜጎች ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ 96 ዜጎች ከታንዛኒያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር ትብብር ማድረጉ ተገልጿል፡፡

በተደጋጋሚ በታንዛኒያ በኩል የሚደረግ ሕገ- ወጥ ፍልሰት÷ ለሞት፣ ለእስር፣ ለአካል ጉዳትና ለእንግልት እየዳረገ መሆኑንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላከተው፡፡

Exit mobile version