አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ሺህ 200 መኖሪያ ቤቶች ግንባታና ዕድሳት መደረጉን የክልሉ ሴቶች ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የሲዳማ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ መድረክ በአለታ ወንዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በማጠቃለያ መርሐ- ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዐቅመ ደካማና ለአረጋውያን ግንባታና ዕድሳት የተደረገላቸውን መኖሪያ ቤቶች እየጎበኙ ነው።
በክልሉ በክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ- ግብር ግንባታና እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለዐቅመ ደካሞችና ለአረጋውያን መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!