አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፈው ዓመት በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ከቀያቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው የነበሩ 4 ሺህ 541 ሰዎች በዛሬው ዕለት ወደ ነበሩበት መመለሳቸውን የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ታደሰ ተናግረዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣የሁለቱ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ባደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ሊመለሱ ችለዋል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።
ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከተመለሱ በኋላ መንግስት ከሚያደረግላቸው ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ ወቅቱ አዝርዕት የሚዘራበት ወቅት በመሆኑ ፈጥነው የሚደርሱ የሰብል ዓነቶችን በማልማት ከመቸውን በላይ የግብርና ስራቸውን አጠናክረው እንዲሰሩ መገለፁን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የቀጠናውን ሰላም ወደ ነበረበት ለማምጣት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት ከተቋቋመ ወዲህ አንጻራዊ ሰላም መመዝገቡን መመሪያሰው ያስታወሰው።

