Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዲፕሎማቶች ማኀበር መመስረት ለብሔራዊ ጥቅም መከበር የጎላ ጠቀሜታ አለው – አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ 

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ማኀበር መመስረት ለብሔራዊ ጥቅም መከበር የጎላ ጠቀሜታ አለው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናገሩ፡፡

ሀገራቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትና በልዩ ልዩ ሃላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎችን ያከተተ የዲፕሎማቶች ማህበር ተመስርቷል፡፡

በማህበሩ ምስረታ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ÷ አንጋፋ ዲፕሎማቶችን እና የአሁኑን ትውልድ የውጭ ጉዳይ ባለሙያዎች ያሰባሰበው ማኀበር መመስረቱ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ።

ማህበሩ በውጭ ግንኙነት ዘርፍ  በጥናት እና ምርምር ፣ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማሳየት እንዲሁም ወጣቶችን በማሰልጠን የእውቀት ሽግግር በማድረግ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።

በማህበሩ ምሥረታ ላይ የተገኙ ዲፕሎማቶች በበኩላቸው ÷ የሙያ ማኀበሩ መመስረቱ የዲፕሎማሲ ሙያ እና ጥበብ እንዲጎለብት እንዲሁም በባለሙያዎች መካከል ማኀበራዊ ትስስር እንዲጠናከር እንደሚያስችል  ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ማህበር መመስረቱ በተደራጀ መልኩ ሙያዊ አስተዋጽኦ ለማድረግ እና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ፋይዳው የጎላ ነው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version