አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በኮፕ28 ‘ግሪን ዞን’ የዱባይ ከተማ ኤክስፖ ላይ ያዘጋጀችው የአረንጓዴ ዐሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) የሚደነቅና በዋናነት የመሪነትን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ ገለጹ።
ዳይሬክተሯ በኮፕ28 ‘ግሪን ዞን’ የዱባይ ከተማ ኤክስፖ ላይ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ጎብኝተዋል።
በአውደ ርዕዩ እስካሁን ያልተነገረና ትልቅ ታሪክ የተመለከቱበት መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሯ ወቅቱ ተግባርን የሚጠይቅ በመሆኑ ለተግባሩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ መመደብ ይገባናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በኮፕ28 ‘ግሪን ዞን’ የዱባይ ከተማ ኤክስፖ ላይ ያዘጋጀችው የአረንጓዴ ዐሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) አስደናቂ ተግባርን የሚያሳይና ሁሉም ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ያመላከተ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ተግባር በአንዲት አፍሪካዊት ሀገር ላይ መጀመሩን ያመላከተ ነው ሲሉም መግለፃቸን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረትና ያላት ቁርጠኝነት የሚታይበትን በኮፕ28 ‘ግሪን ዞን’ የዱባይ ከተማ ኤክስፖ ላይ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መካነ ርዕይ(ፓቪሊዮን) በተለያዩ ሀገራትና ተቋማት መሪዎች እየተጎበኘ ይገኛል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!