Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉና አቶ ታደሰ ለማ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ ሰብሳቢ ሆነው ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ እና አቶ ታደሰ ለማ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ ሰብሳቢ ሆነው መቅረባቸው ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ መሰየማቸው ይታወሳል።

ኮሚቴው እስካሁን ያከናወናቸውን ተግበራት በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ኮሚቴው ባደረገው የጥቆማ መቀበል ሒደት ከደረሱት 56 ጥቆማዎች መካከል ለመጨረሻ ዙር አምስት መለየታቸውን ገልጿል።

ከ5ቱ መካከልም ኮሚቴው በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ሁለቱን ለመጨረሻ ዙር ለይቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማቅረቡን አስታውቋል።

በዚህም ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ አበበ እና አቶ ታደሰ ለማ ገርቢ መስፈርቱን አሟልተው መለየታቸውን ነው ኮሚቴው የገለጸው።

የልየታ ሒደቱ ብርቱ ጥንቃቄ የተደረገበት እና ኮሚቴው በትኩረት የሰራበት ስለመሆኑም ተነግሯል።

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ሁለቱ ዕጩዎች መካከል አንድ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ በፓርላማ ቀርቦ እንደሚሾም መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version