አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀረ-አበረታች ቅመሞችን ሕግ ተላልፈዋል በተባሉ ስምንት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በተጨማሪ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ እና ፀሐይ ገመቹ ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ ጊዜያዊ እገዳ ተጥሎባቸው ጉዳያቸው በመጣራት መሆኑን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡
ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው÷ በ2023 በተካሄዱ ምርመራዎች 10 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን በመጠቀም ተጠርጥረው ጉዳያቸው ሲጣራ ቆይቷል።
በዚሁ መሠረት ስምንት አትሌቶች የሕግ ጥሰት መፈፀማቸው በመረጋገጡ በአማካኝ ከ 1ዓመት ተኩል እስከ 4 ዓመት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር እንዳይሳተፉ አሥተዳደራዊ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ብሏል፡፡
እንዲሁም የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን በመሸጥ ብሎም ሞያቸውን ተገን በማድረግ ለአትሌቶች በመስጠት የሕግ ጥሰት በፈፀሙ መድኃኒት ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብሏል ባለስልጣኑ፡፡
በሕግ ጥሰቱ ውስጥ የተሳተፉ አከላትም ጉዳያቸው በሕግ መያዙን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሕገ-ወጦችን የማረምና የማስተካከል ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያሳሰበው ባለስልጣኑ÷ ችግሩን ከሥሩ ለመቅረፍም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!