Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች እና ወ/ሮ ሙፈሪሃት ለሚ እንጀራ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ለሚ የእንጀራ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ሴቶች አበረታተዋል፡፡

ፋብሪካው ለሴቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ ጥራቱን የጠበቀ ምርት ማቅረቡን ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ፋብሪካው ገበያ በማረጋጋት ረገድ ዓይነተኛ ሚና እንዲጫወት የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር የገበያ ትስስሩን ማጠናከር ላይ እንደሚሠራ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ተናግረዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version