አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን በመተሃራ እና በወለንጪቲ መሃል በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት በወደቀ ተሽከርካሪ ቦቴ የተዘጋው መንገድ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
አደጋ ምክንያት የተዘጋውን መንገድ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ትናንት መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
በመሆኑም የከፍተኛ ተሽከርካሪዎች መተላለፊያ የሆነውን የኢትዮጂቡቲ መስመር ለማስከፈት በተደረገው ጥረት ከምሽት 11 ሰዓት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ማድረግ መቻሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በአሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ዋና መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር በላቸው ትኪ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የወደቁ መኪኖችን ከመስመሩ በማንሳት መንገዱ እንዲከፈት ተደርጓል፡፡
በሚኪያስ አየለ