አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቤላ የሕጻናትና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።
ከንቲባ አዳነች በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መሰል የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በመገንባት ትውልዱን በስፖርትና በሥነ-ምግባር የዳበረ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ከ1 ሺህ 100 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የወጣቶችና ሕጻናት ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የማስፋፋት ሥራችንን የጣሊያን ኤምባሲ በመደገፍ ዛሬ የመረቅነውን የስፖርት ማዘውተሪያ በመገንባቱ እናመሠግናለን ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባን ሕጻናት ቦርቀው፣ ደስ ብሏቸው፣ በአእምሮ እና በአካል ጎልብተው የሚያድጉባት ከተማ ለማድረግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡
የቤላ የሕጻናትና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያው÷ የእግር ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የቮሊቦል መጫዎቻ ሜዳና ሌሎችንም ያካተተ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!