Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መኖሪያ ቤት ውስጥ በተነሳ እሳት እናትና የአንድ ዓመት ልጅ ህይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ አማን ቀበሌ ቀጠና 02 ልዩ ስሙ ሻሻቃ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተነሳ እሳት እናትና የአንድ ዓመት ልጅ ህይወት አለፈ፡፡

አደጋዉ የደረሰው ዛሬ 3 ሰዓት አካባቢ በህገወጥ መንገድ በመኖሪያ ቤት ዉስጥ ለሽያጭ የተዘጋጀ 4 በርሜል ቤንዚን ከኤሌክትሪክ ምድጃ አጠገብ በመቀመጡ በተነሳ እሳት መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም እናትና የአንድ ዓመት ልጅ ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ከባድ እና በሰባት ዓመት ታዳጊ ላይ ቀላል ቃጠሎ እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ ተናግረዋል።

ቃጠሎ ለደረሰባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ እና በቃጠሎዉ የወደመ ንብረት እየተጣራ መሆኑን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version