Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ በኋላ በተሟላ መንገድ ወደ ስራ መግባት ተችሏል – አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምስረታ በኋላ በተሟላ መንገድ ወደ ስራ መግባት እንደተቻለ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው÷ በየደረጃው ካሉ የሥራ ሀላፊዎች ጋር በ100 ቀናት እቅድ ትግበራ ላይ ውይይት እያካሔዱ ነው፡፡

አቶ እንዳሻው በውይይት መድረኩ እንደገለጹት፥ በክልሉ አበይት ተግባራትን በመለየት ወደ ስራ መግባት ተችሏል።

ከክልሉ ምስረታ በኋላ የ100 ቀናት እቅድ በማዘጋጀት አመራር ከማደራጀት ጀምሮ የመንግስት ስራዎችን መምራት፣ ክልሉን ማደራጀት እና ዞኖችን በማጠናከር ወደ ስራ መግባት መቻሉንም ጠቁመዋል።

በክልሉ በጸጥታ፣ በግብርና፣ በገቢ፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፍ የሚተገበሩ ስራዎች ላይም በማተኮር መስራት መቻሉን አብራርተዋል።

መድረኩ የተከናወኑ ተግባራትን አፈጻጸም በመገምገም ለተሻለ ለውጥ መትጋት የሚያስችል እንደሆነ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የተከናወኑ ስራዎችን መሰረት በማድረግ በሚቀጥሉት 100 ቀናት የሚተገበሩ ተግባራትን ማቀድ የሚያስችል ሙሉ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version