አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በደቡብ ምዕራብ ክልል የሚገኘውን ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 የስኳር ፋብሪካዎችን ጎብኝቷል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ቡድን አስተባባሪ አቶ ኢያሱ ዛላ በፕሮጀክቱ ዙሪያ ያለውን ችግር በአንድ ጊዜ መፍታት ስለማይቻል ቅድሚያ በሚሰጡ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስገንዝበዋ፡፡
ችግሮችን ለመቅረፍም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር÷ ከወረዳ፣ ዞን እና ክልል አስተዳዳሪዎች ጋር የጋራ እቅድ በማውጣት መስራት እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ የፋይናንስ ችግር እንዲፈታም ለሚመለከተው አካል እንደሚያቀርቡ እና የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ኢያሱ አረጋግጠዋል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳግማዊ በየነ (ኢ/ር) በበኩላቸው÷ የአገዳ እንክብካቤ እና ቆረጣ ሥራ ለመሥራት የቀን ሠራተኛ አለመኖር፣ የመለዋወጫና ጎማ ዋጋ የውጭ ምንዛሬ መጨመር፣ ለሚተከሉና ለተተከሉት አገዳዎች በቂ ውኃ ባለመገኘቱ የአገዳ ምርታማነት መቀነስ፣ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በተለያዩ ምክንያቶች መልቀቃቸውና የውሃ ማጠጫ መስመር በአካባቢው ማህበረሰብ ተቆርጦ እየተወሰደ ስለሆነ ተቸግረናል ብለዋል።
የማጂ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስ ኃላፊ አቶ በድሉ ታደመ÷ በፕሮጀክቶች አካባቢ ያለው መሰረተ ልማት እንዲስተካከል በጋራ እንሠራለን ብለዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!