አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአሜሪካ አትላንታ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀረ-ሙስና ስምምነት የአባል ሀገራት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
በጉባዔው ላይ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
የአባል ሀገራት የፀረ-ሙስና ስምምነት አፈጻጸም ላይ ጉባዔው እንደሚመከር እና አባል ሀገራቱም የፀረ-ሙስና ትግል ትብብርን ለማጠናከር የሚያግዙ ምክክሮችን እያደረጉ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በጉባዔው ላይም የኢትዮጵያ ሀገራዊ የፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ ሪፖርት መቅረቡን የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
በየሁለት ዓመት የሚካሄደውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ጉባዔም ኢትዮጵያ የምታዘጋጅበት ዕድል እንዲሰጥ ኮሚሽነሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ጥያቄውንም በጉባዔው ሥራ አስፈጻሚ ለማየት አወንታዊ ምላሽ ተገኝቷል ተብሏል።
በሌላ በኩል ከሀገር የሚሸሽ ሀብትን ለማስመለስ የሀገራትን ትብብር የሚያጠናክሩ የጎንዮሽ ምክክሮች እየተካሄዱ መሆኑ ተገልጿል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!