አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ተለያዩ ሀገራት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓዙ የነበሩ 134 ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከኬንያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ተመላሾቹ ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ ሳይኖራቸው በደላሎች ተታለው በሕገ-ወጥ መንገድ ኬንያን መሸጋገሪያ በማድረግ ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲያቀኑ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ በኬንያ ናይሮቢ፣ ሞምባሳ፣ ማቻኮስ ካውንቲ እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች በሚገኙ እስር ቤቶች ታስረው እንደነበር ተገልጿል፡፡
በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኬንያ ፖሊስና ኢሚግሬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር 134 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡