Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ማስፈጸሚያ ከ36 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጽድቋል።

በጀቱ የጸደቀው በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።

በምክር ቤቱ የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዕንቁ ዮሐንስና የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በጋራ የክልሉን የስራ ዘመኑ በጀት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

በጀቱ የክልል ማዕከልና የ12 ዞኖች ለመንግስት የመደበኛና ካፒታል ሥራዎች እንደሚውል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version