አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ባደረገው ጥሪ መሰረት ነው ባንኩ ድጋፍ ያደረገው ተብሏል፡፡
ድጋፉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አክሊሉ ውበት (ዶ/ር) ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል፡፡
ባንኩ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ የወጋገን ባንክ ሰራተኞች በግላቸው 100 ኩንታል የእህል ድጋፍ አድርገዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!