Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 839 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
 
ተመራቂዎቹ በተለያዩ የሙያ መስኮች በአንደኛ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡
 
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዛይድ ነጋሽ (ዶ/ር)፣ ከፌደራል እና ከክልል የመጡ እንግዶች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 

ዩኒቨርስቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጦርነቱ ወቅት ደርሶበት የነበረውን ጉዳት ጥገናና እድሳት በማድረግ ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው መግባቱ ይታወሳል፡፡

 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version