Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮ- ጃፓን የኢንቨስትመንት ፎረምና የፖለቲካ ምክክር በመጪው የካቲት በቶኪዮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱጂ ኪዮቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በፈረንጆቹ ከፊታችን የካቲት 26 እስከ 29 ቀን ድረስም የኢትዮ-ጃፓን የፖለቲካ ምክክር እንዲሁም የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በቶኪዮ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን አምባሳደር ዳባ ተናግረዋል፡፡

ለፎረሙ ስኬታማነትም በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሱጂ ኪዮቶ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ልማት ጃፓን የምታደርገውን ተሳትፎ እና ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

በሁለቱ ሀገራት በቀጣይ ለሚካሄደው የፖለቲካ ምክክር በጃፓን በኩል አስፈላጊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።

Exit mobile version