Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

1 ሺህ 521 የአሸባሪው ሸኔ አባላት የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በኦሮሚያ ክልል ሲንቀሳቀሱ የቆዩ 1 ሺህ 521 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ለሁለት ወራት የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸው ተገለጸ።

ለሰልጣኞቹ በቢሻን ጉራቻ ከተማ ቶጋ ካምፕ የቃለ መሐላና የይቅርታ መርሐ- ግብር ተካሂዷል።

ቀደም ሲል በስህተት የትጥቅ ትግል ለማድረግ ጫካ ገብተው ለቆዩ፣ በፈቃዳቸውና ተማርከው እጃቸውን ለመንግሥት በመስጠት በቁጥጥር ስር ለዋሉ 1 ሺህ 521 የሽብር ቡድኑ አባላት የሁለት ወራት የተሃድሶ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

ስልጠናውም በሀገሪቷ ባሉ ተጨባጭ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት መብራራቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተሃድሶ ስልጠናውን የወሰዱ የቀድሞ የአሸባሪው ሸኔ አባላት በትጥቅ ትግል ስም በፈጸሙት ጥፋት መጸጸት ብቻ ሳይሆን ተመልሰው ተመሳሳይ ዓይነት ስህተት ላለመፈጸም ቃል መግባታቸውም ነው የተመለከተው፡፡

እንዲሁም በየትኛውም ዓይነት ግጭት ውስጥ ራሳቸውን ባለማስገባት ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው በሰላም ሠርተው ለመኖር ወስነዋል ተብሏል፡፡

Exit mobile version