አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን ከሕጋዊ አሰሪዎቻቸው ውጭ እየሠሩ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሕጋዊ ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ተጠየቀ፡፡
በባህሬን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ ከሀገሪቱ የሠራተኞች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኒብራስ መሀመድ ታሊብ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይታቸው በባህሬን ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የመብት ጥበቃ እና ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው እየሰሩ የሚገኙ ዜጎች ህጋዊ መሆን በሚችሉባቸው አማራጮች ላይ ያተኮረ ነበር።
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ከሚሠሩባቸው ቦታዎች ጠፍተው ከሕግ አግባብ ውጭ እየሠሩ እንደሚገኙ አምባሳደር ሽፍራው በውይይታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡
ስለሆነም ይቅርታ ተደርጎላቸው ሕጋዊ እንዲሆኑ በተቋሙ በኩል ሁኔታዎች እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል፡፡
ኒብራስ መሀመድ ታሊብ በበኩላቸው÷ ሕጋዊ አሠራርን ጥሰው ከአሠሪዎቻቸው ውጭ እየሠሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተም ሠራተኞቹ ከአሠሪዎቻቸው የጠፉበትን ምክንያት በማስረዳት ትክክለኛነቱ ተረጋግጦ ሕጋዊ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ ይከናወናል ብለዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!