አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ካሊፎርኒያ የስልጠና ተቋም በዲጂታል ማርኬቲንግ የተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የኢትዮ ቴሌኮም አመራሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ተቋሙ አሁን ላይ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ዘርፍ ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ባለሙዎችን እያፈራ እንደሚገኝ የተቋሙ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል አባይነህ ገልጸዋል።
ተቋሙ ከዲጂታል ማርኬቲንግ በተጨማሪ በሳይበር ደህንነት፣ በድረገጽ ዴቨሎፕመንት፣ በኮዲንግ፣ በፕሮግራሚንግና ተያያዥ ዘርፎች ብቁ ባለሙያዎችን እያፈራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሥልጠናው በመደበኛ፣ በማታና በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ቅዳሜና እሑድ በአጫጭር ኮርሶች ለወራት እንደሚሰጥ ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።
ተቋሙ በቀጣይ ዘመኑን የዋጁ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሰራም ጠቅሰዋል።
ለሰለጠኑ ባለሙያዎች የሥራ እድል ከመፍጠር አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አንስተዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ለማጠናከር ተቋሙ የበኩሉን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል።