Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ግዥ ተፈፅሞ እየተጓጓዘ መሆኑን የአማራ ክልል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ግዥ ተፈፅሞ እየተጓጓዘ መሆኑን አማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አጀበ ስንሻው አስታወቁ፡፡

ተገዝቶ ወደብ ከደረሰው 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ውስጥ 718 ሺህ ኩንታል እየተጓጓዘ መሆኑንና እስካሁንም 547 ሺህ ኩንታል በዩኒየኖች ማዕከላዊ መጋዝኖች ደርሶ መራገፉን ነው ምክትል ኃላፊው የገለጹት፡፡

ማዳበሪያውም ለመስኖ ልማት እንዲውል ለአርሶ አደሩ ፈጥኖ እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው÷ የከረመውን ጨምሮ እስካሁን ከ92 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ መሰራጨቱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ተገዝቶ እየተጓጓዘ ያለው የአፈር ማዳበሪያም ባለፈው ዓመት ከቀረበው ጋር ሲነፃፀር ከ3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version