አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ ዐቅማቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን ተናገሩ፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጎንደር ከተማ በኢንቨስትመንት መንደሮች የሚገኙ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የምርት እንቅስቃሴና የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡
በክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የጸጥታ ችግር ሳይበግሯቸው እያከናወኑት ያለው የምርት እንቅስቃሴ የሚያበረታታ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምሮ ወደ ውጪ በመላክ የሀገሪቱን የወጪ ምርት ዐቅም በማሳደግና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ተክቶ በማምረት በኩል በክልሉ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት አምራች ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን የኃይል አቅርቦት ችግር ከመፍታት ጀምሮ ለግንባታ ቦታ አቅርቦት ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በኩል በትኩረት እንደሚሠራም ነው የተናገሩት፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች በተረጋጋ መንገድ የምርት እንቅስቃሴያቸውን እንዲያከናውኑ ለማስቻል አሁን ያለውን ሰላም ወደ ዘላቂነት ለማሸጋገር የሚያስችሉ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በጎንደር ከተማ በተቋቋሙ አምስት የኢንዱስትሪ መንደሮች 180 አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት ሥራ መግባታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ግርማይ ልጃለም ገልጸዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

