Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፌዴራል ፖሊስ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ለመጨረሻ ጊዜ ውይይት ተካሄደበት

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ለመጨረሻ ጊዜ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጀው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ÷ ለሁለት ዓመታት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሲዘጋጅ የቆየው አዋጁ ለመጨረሻ ጊዜ ለውይይት መቅረቡን ተናግረዋል።

ረቂቅ አዋጁ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እንደሀገር እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊትን ሥራ ለማቅለልም ይረዳል ነው ያሉት፡፡

በውይይቱ ላይ የፍትሕ ሚኒስትር፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች መሳተፋቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ÷ የተሻሻለው የፖሊስ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ፀድቆ ወደ ተግባር ሲገባ የህዝብን ደህንነት ለማስፈን፣ ልማትን ለማፋጠን እና የፖሊስ ሠራዊትን ለመገንባት እንደሚያግዝም ነው ያነሱት፡፡

Exit mobile version