Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመውሊድ በዓል አከባበር ስነ-ስርዓትን በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውሊድ በዓል አከባበር ስነ-ስርዓትን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ያለመ የጥናት ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ባህላዊ መልኮችን በማጥናት ይህን መልኩን ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ሶስት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን÷ የእምነቱ ተከታዮች እና መምህራንን ጨምሮ በርካታ አካላት በውይይቱ መድረኩ ተሳትፈዋል።

የጥናት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩን ያዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ነው።

በበረከት ተካልኝ

Exit mobile version