Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንክብካቤና የልማት ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያና ውስጥ ለውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ቀደም ሲል የነበረውን የ’አይቻልም’ እሳቤን የቀየረ ነው ብለዋል።

በሁለተኛው ዙር የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የልማት ስራ በወቅቱ ጀምረው አበረታች ስራ እያከናወኑ የሚገኙ ተቋማትን አበረታተዋል።

ወደ ስራ ያልገቡ ተቋማት በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ተቋማቱ በሚያከናውኗቸው የግንባታ ስራዎችም ጥራት፣ ፍጥነትና ውበትን ታሳቢ በማድረግ መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠው፤ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ሁሉም ባለድርሻ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version