Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግልፅነት ያለው የፋይናንስ አስተዳደር እንዲኖር አመራሩ ስራውን በአግባቡ ሊከታተል እንደሚገባ ተጠቆመ

 አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግልፅነት ያለው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር እንዲኖር አመራሩ ስራውን በአግባቡ ተገንዝቦ ሊመራ፣ ሊደግፍና ሊከታተል እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ባዘጋጁት መድረክ ላይ በባስተላለፉት መልዕክት÷ በክልሉ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ትግበራ የተቀመጡትን መሰረታዊ ግቦች ማሳካት መቻሉን አንስተዋል፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም በአንዳንድ ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ የአሰራር ክፍተት መኖሩን ነው የገለጹት።
በተለይም የውስጥ ኦዲት ትግበራ፣ የመንግስት ንብረት ግዢና የበጀት አጠቃቀም ላይ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በሪፎርሙ የተቀመጡ ደንብና መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡቦንግ ኡቶው በበኩላቸው÷ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት በክልሉ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ ወጥነት ያለው የበጀት አወቃቀር እንዲኖር፣ የበጀትና የሂሳብ አሰራር ዘመናዊ እንዲሆን እና የዜጎችን የመረጃ ተደራሽነት ያሳደገ መሆኑን አብራርተዋል።
የመንግስት ፋይናንስ ስርዓትን በተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ ማድረጉ የበጀት አጠቃቀምን ከማሻሻል ባለፈ በጀትን ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚረዳ እንደሆነ መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version