Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ በጎዴ ከተማ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በጎዴ ከተማ እየተካሄዱ የሚገኙ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተግልጿል፡፡

የፕሮጀክቶቹ ግንባታ መጠናቀቅም የከተማውን ልማትና ዕድገት በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መገለጹን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

በሸበሌ ዞን ጎዴ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ 18 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ 8 የመንገድ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡

በተመሳሳይ በአቶ ሙስጠፌ የተመራ የአመራሮች ልዑክ በዋቢ ሸበሌ ወንዝ አካባቢ በመከናወን ላይ የሚገኙ የእርሻ ልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡

Exit mobile version