Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትምህርት ሚኒስቴር 37 የሞተር ብስክሌቶችን ለጋምቤላ ክልል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር 37 የሞተር ብስክሌቶችን ለጋምቤላ ክልል ድጋፍ አደርጓል።

በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ሸዋረገጥ (ዶ/ር) በርክክቡ ወቅት÷ የሞተር ብስክሌቶቹ ለጋምቤላ ከተማ አስተዳደር እና ለሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች የተከፋፈሉ ሲሆን ለክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚውሉም ገልጸዋል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ድጋፉን የተረከቡት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ላክዴር ላክባክ የሞተር ብስክሌቶቹን በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ለጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ያስረከቡ ሲሆን÷ ድጋፉ የትምህርት ዘርፉን ከማሳለጥ አንፃር ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

በተለይ ለወረዳና ለዞን የትምህርት ባለሙያዎች ጠቀሜታው የላቀ እንደሆነ ጠቅሰው ፣ በውሎ ገብ የሚሰሩ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖራቸውም ማስረዳታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሞተር ብስክሌቶቹ ለ13 ወረዳዎች፣ ለሶስት ዞኖችና ለጋምቤላ ከተማ አስተዳደር እንዲከፋፈሉ መደረጉን የገለፁት አቶ ላክዴር ለትምህርት አገልግሎት ብቻ ሊውሉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version