አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቅንጅታዊ አቅምን በማጎልበት እና አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና “የብልጽግና ተምሳሌት ከተማ ግንባታ አመራር ሚናዎች ፣ኃላፊነቶች እና ስብዕናዎች” በሚል ርዕስ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው የከተማ ተለዋዋጭ ባህርይ፣ ሕብራዊነት፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችንና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ባለራዕይ አመራር ለመፍጠር ያለመ ነው መባሉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
አመራሩ በነዋሪው ዘንድ አመኔታን እና እርካታን የሚፈጥር እንዲሆን ለማድረግ፥ በአመራር ዘይቤ እና ስብዕናዎች ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱም ነው የተገለጸው።
ከተማዋን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እና የልማት አቅሞችን በማስተባበር አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን፣ የአመራሩን እና ሰራተኛውን ቅንጅታዊ አቅም ለማጎልበት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!