Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ስራዎችን ማከናወን ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸሩጌታ ገነነ ገለጹ።
 
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ስራዎች ያመጡትን ለውጦች ለማወቅ ባስጠናው ጥናት ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የሚያስችል የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ እያካሄደ ነው።
 
በመድረኩ የተገኙት ሚኒስትር ዴኤታው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ በሰላም ግንባታና በሌሎች ዘርፎች ላይ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።
 
የሰላም ግንባታ ስራዎች በአንድ ተቋም ብቻ የሚከናወኑ ሳይሆኑ ሁሉንም ያማከሉ ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
 
የሶማሌ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደይብ አህመድኑር በበኩላቸው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በጋራ መስራት ወሳኝ መሆኑን ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ሶማሌ ክልል ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመቻቸል በአብሮነትና በሰላም የሚኖሩበት መሆኑን ጠቁመው፥ በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት በተፈጠረው ሰላም የልማትና ስራዎች በፍጥነት ማደጋቸውን ነው የገለጹት።
 
በመድረኩ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ተገኝተዋል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version