Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል ገበያውን ለማረጋጋት 600 ሚሊየን ብር ተመድቦ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ገበያውን ለማረጋጋት 600 ሚሊየን ብር ተመድቦ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ እንደ ክልል የተከናወኑ የገበያ ማረጋጋት ሥራዎች በጎንደር ከተማ እየተገመገሙ ነው።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ብዙዓለም ግዛቸው ከግምገማው ጎንለጎን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ቢሮው ገበያውን ለማረጋጋት ለክልሉ መንግስት 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ጥያቄ አቅርቦ 600 ሚሊየን ብር ተፈቅዶለት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

በተጨማሪም 800 ሚሊየን ብር በተዘዋዋሪ ብድር እንዲጠቀም መፈቀዱን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣዮቹ ሥድስት ወራትም ሸማች ተኮር የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የግብርና ምርቶች ወደ ገበያ እንዲገቡ በልዩ ትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡

አዳዲስ የመሠረታዊ ፍጆታ አምራቾች ወደ ሥራ እንዲገቡም ሥራዎች ይከናወናሉ ነው ያሉት፡፡

የክልሉ መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት ከመደበው 600 ሚሊየን ብር በተጨማሪ ከተሞች ከ20 እስከ 60 ሚሊየን ብር መድበው እንዲሠሩ አቅጣጫ መቀመጡን አመላክተዋል፡፡

በበላይነህ ዘላለም

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version